ዘኍል 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገር ልጅ ሁሉ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ቍርባን ባቀረበ ጊዜ እንዲሁ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም የአገር ተወላጅ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች በዚሁ ሁኔታ ያድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአገሩ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ባቀረበ ጊዜ እነዚህን ነገሮች እንዲሁ ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአገር ተወላጅ የሆነ እያንዳንዱ እስራኤላዊ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የእህል ቊርባን በሚያቀርብበት ጊዜ ይህን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገር ልጅ ሁሉ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ባቀረበ ጊዜ እንዲሁ ያደርጋል። |
መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል።