Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 15:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ማንኛውም የአገር ተወላጅ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች በዚሁ ሁኔታ ያድርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የአገሩ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ባቀረበ ጊዜ እነዚህን ነገሮች እንዲሁ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የአገር ተወላጅ የሆነ እያንዳንዱ እስራኤላዊ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የእህል ቊርባን በሚያቀርብበት ጊዜ ይህን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የሀ​ገር ልጅ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ቍር​ባን ባቀ​ረበ ጊዜ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የአገር ልጅ ሁሉ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ባቀረበ ጊዜ እንዲሁ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 15:13
2 Referencias Cruzadas  

ባዘጋጃችሁት ቍጥር ልክ ይህን ለእያንዳንዱ አድርጉ።


ለሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ መጻተኛ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም ሰው በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos