ሎሌውም፥ “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው አቀርባለሁ?” አለ። እርሱም፥ “ይበላሉ፥ ያተርፋሉም ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአልና ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው” አለው።
ዘኍል 11:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴ ያለቅሳሉና፦ የምንበላውን ሥጋ ስጠን ይላሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምሰጠው ሥጋ ከየት አለኝ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዚህ ሁሉ ሕዝብስ ሥጋ ከወዴት አመጣለሁ? ሁሉም ‘የምንበላው ሥጋ ስጠን’ እያሉ ያለቅሱብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በፊቴ እያለቀሱ እንዲህ ይላሉና፦ ‘የምንበላውን ሥጋ ስጠን’፤ እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምሰጠው ሥጋ ከወዴት አገኛለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምንበላውን ሥጋ ስጠን እያሉ ወደ እኔ መጥተው ስለሚያለቅሱ ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ የሚሆን ሥጋ ከወዴት አመጣለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊቴ ያለቅሳሉና፦ የምንበላውን ሥጋ ስጠን ይላሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምሰጠው ሥጋ ከወዴት እወስዳለሁ? |
ሎሌውም፥ “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው አቀርባለሁ?” አለ። እርሱም፥ “ይበላሉ፥ ያተርፋሉም ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአልና ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው” አለው።
ንጉሡም በእጁ ተደግፎት የሚቆም የነበረ ያ ብላቴና ለኤልሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ የእህል ሿሿቴ ቢያደርግ ይህ ነገር ይሆናልን?” አለው። ኤልሳዕም፥ “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፤ ከዚያ ግን አትቀምስም” አለ።
ነገር ግን በመካከላችሁ ያለውን እግዚአብሔርን ንቃችኋልና፥ በፊቱም፦ ለምን ከግብፅ አወጣኸን? ብላችሁ አልቅሳችኋልና በአፍንጫችሁ እስኪወጣ መርዝም እስኪሆንባችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበሉታላችሁ።”
ሙሴም፥ “እኔ በመካከላቸው ያለሁ ሕዝብ ስድስት መቶ ሺህ እግረኛ ናቸው፤ አንተም፦ ሥጋን እሰጣቸዋለሁ፥ ወር ሙሉም ይበሉታል አልህ።