ነህምያ 13:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልጆቻቸውም እኩሌቶቹ በአዛጦን ቋንቋ ይናገሩ ነበር፤ በሌሎች ሕዝብ ቋንቋ የሚናገሩም ነበሩ፤ በአይሁድም ቋንቋ መናገር አያውቁም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከልጆቻቸውም እኩሌቶቹ የአሽዶድን፣ ወይም ከሌሎቹ ሕዝቦች የአንዱን ቋንቋ እንጂ ዕብራይስጥ መናገር አይችሉም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከልጆቻቸውም እኩሌቶቹ በአዛጦን ቋንቋ ይናገሩ ነበር፥ በአይሁድም ቋንቋ መናገር አያውቁም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኩሌቶች ልጆቻቸው የአሽዶድንና የሌሎችንም አንዳንድንም ቋንቋዎች ይናገሩ ነበር፤ የአይሁድን ቋንቋ መናገር ተስኖአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከልጆቻቸውም እኩሌቶቹ በአዛጦን ቋንቋ ይናገሩ ነበር፥ በአይሁድም ቋንቋ መናገር አያውቁም ነበር። |
እነርሱንም ተቈጣኋቸው፤ ረገምኋቸውም፤ ከእነርሱም ዐያሌዎቹን መታሁ፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፥ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።