ከዚህ በኋላ ሰንበት ከመግባቱ በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖች በዐያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ።
ነህምያ 13:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ከኢየሩሳሌም ውጭ አድረው ገበያ አድርገው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልዩ ልዩ ሸቀጣ ሸቀጥ ነጋዴዎችና ቸርቻሪዎች ከኢየሩሳሌም ውጭ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ዐድረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በኢየሩሳሌም ውጭ አድረው ገበያ አድርገው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየዐይነቱ ሸቀጣሸቀጦችን ለሺያጭ የሚያቀርቡ ነጋዴዎች ለአንድ ጊዜም ለሁለት ጊዜም የሰንበት ዋዜማ የሆነውን የዓርብን ምሽት ከከተማይቱ ቅጽር ውጪ አሳለፉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በኢየሩሳሌም ውጭ አድረው ገበያ አድርገው ነበር። |
ከዚህ በኋላ ሰንበት ከመግባቱ በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖች በዐያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ።
እኔም አስመሰከርሁባቸውና፥ “ከቅጥሩ ውጭ ለምን ታድራላችሁ? እንደ ገና ብታደርጉት እጆችን አነሣባችኋለሁ” አልኋቸው። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ በሰንበት ቀን እንደ ገና አልመጡም።