ሚክያስ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ ትበል፥ ጠላቶችህም ሁሉ ይጥፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤ ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን ይላል ጌታ፦ ፈረሶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ሰረገሎችህንም እደመስሳለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ኀይል በጠላቶቹ ላይ ይነሣል፤ ጠላቶቹም ሁሉ ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ ትበል፥ ጠላቶችህም ሁሉ ይጥፉ። |
እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፤ አግልሻለሁ፤ ዝገትሽንም አነጻለሁ፤ ቆርቆሮሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ፤ ዐመፀኞችን አጠፋለሁ፤ ሕገ ወጦችንም ከአንቺ አስወግዳለሁ፤ ትዕቢተኞችንም አዋርዳለሁ።
በባሕርም በኩል በፍልስጥኤማውያን መርከቦች ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፤ የምሥራቅ ሰዎችንና ኤዶምያስን በአንድነት ይዘርፋሉ፤ በሞዓብ ላይ ቀድመው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ የአሞንም ልጆች ቀድመው ለእነርሱ ይታዘዛሉ።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፣ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።