ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ ባዕዳን ይበሉታል፤ ጠላትም ያጠፋዋል፤ ባድማም ያደርገዋል።
ሚክያስ 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድርህንም ከተሞች አጠፋለሁ፥ ምሽጎችህንም ሁሉ አፈርሳለሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድራችሁን ከተሞች እደመስሳለሁ፤ ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስማትን ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ጠንቋዮችም ለአንተ አይሆኑም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድራችሁ የሚገኙትን ከተሞች አጠፋለሁ፤ ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈራርሳለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድርህንም ከተሞች አጠፋለሁ፥ ምሽጎችህንም ሁሉ አፈርሳለሁ፥ |
ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ ባዕዳን ይበሉታል፤ ጠላትም ያጠፋዋል፤ ባድማም ያደርገዋል።
ሕዝቡን የያዕቆብን ቤት ትቶአልና፤ ምድራቸው እንደ ቀድሞው እንደ ፍልስጥኤማውያን ምድር በሟርት ተሞልቶአልና፤ እንደ ባዕድ ልጆችም ሆነዋልና፤ ብዙ እንግዶች ልጆችም ተወልደውላቸዋልና።
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፥ “ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ፥ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ ነው፤”
ቤት። እግዚአብሔር የያዕቆብን መልካም ነገር ሁሉ አሰጠመ፤ አልራራምም፤ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አንባዎች አፈረሰ፤ ወደ ምድርም አወረዳቸው፤ መንግሥቷንና ግዛቷንም አረከሰ።
ወደ ጠፋች ሀገር እወጣለሁ፤ ተዘልለው በሰላም ወደሚኖሩ፥ ሁላቸው ሳይፈሩ ያለ ቅጥርና ያለ መወርወሪያ፥ ያለ መዝጊያም ወደሚቀመጡባት ምድር እገባለሁ፤
በሕዝብህም መካከል ጥፋት ይነሣል፤ እናትም በልጆችዋ ላይ በተጣለች ጊዜ የሰልማን አለቃ ቤትአርብኤልን በጦርነት ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።