ምድራቸውም በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ለመዛግብቶቻቸውም ቍጥር የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፤ ለሰረገሎቻቸውም ቍጥር የለውም።
ሚክያስ 5:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ፈረሶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ሰረገሎችህንም እሰብራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁን እደመስሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድርህን ከተሞች አጠፋለሁ፥ ምሽጎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀደም ብዬ ግን ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ፈረሶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ሰረገሎችህንም እሰብራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ |
ምድራቸውም በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ለመዛግብቶቻቸውም ቍጥር የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፤ ለሰረገሎቻቸውም ቍጥር የለውም።
በእውነት የተራሮች ኀይል፥ የኮረብቶችም ኀይል ሐሰት ነው፤ ነገር ግን የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
ነገር ግን የይሁዳን ልጆች ይቅር እላቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸውም እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት ወይም በሰይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠረገላ፥ ወይም በፈረሶች፥ ወይም በፈረሰኞች የማድናቸው አይደለም” አለው።
ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ። እንዲህም በሉት፥ “ኀጢአትን ሁሉ አስወግድ፤ በቸርነትም ተቀበለን፤ በወይፈንም ፈንታ የከንፈራችንን ፍሬ ለአንተ እንሰጣለን።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፣ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።
ለእርሱ ፈረሶችን እንዳያበዛ፥ ሕዝቡንም ወደ ግብፅ እንዳይመልስ፤ እግዚአብሔር፦ በዚያች መንገድ መመለስን አትድገም ብሎአልና።