ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፤ ብላቴናይቱም ተነሣች።
ሕዝቡም ከወጣ በኋላ ወደ ውስጥ ገብቶ እጇን ያዘ፤ ብላቴናዪቱም ተነሥታ ቆመች።
ነገር ግን ሕዝቡን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፤ ልጅቱም ተነሣች።
ሰዎቹም ከወጡ በኋላ፥ ኢየሱስ ልጅትዋ ወደምትገኝበት ክፍል ገብቶ እጅዋን ያዛት፤ እርሷም ተነሣች።
ሕዝቡን ግን ከአስወጡ በኋላ ገብቶ እጅዋን ያዛት፥ ብላቴናይቱም ተነሣች።
ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።
የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ፍችውም “አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ!” ነው።
ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፤ በዐይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት “አንዳች ታያለህን?” ብሎ ጠየቀው።
ኢየሱስ ግን እጁን ይዞ አስነሣው፤ ቆመም።
እርሱ ግን ሁሉን ወደ ውጭ አስወጣና እጅዋን ይዞ ጠራት፤ እንዲህም አላት፥ “ አንቺ ብላቴና ተነሺ።”