La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 8:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አጋንንቱም “ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። “ሂዱ፤” አላቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አጋንንቱም ኢየሱስን፣ “የምታስወጣን ከሆነ ዐሣማዎቹ መንጋ ውስጥ እንድንገባ ፍቀድልን” ብለው ለመኑት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ፥ ወደ ዓሣማው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ፥ እባክህ ወደዚያ ወደ ዐሣማዎቹ መንጋ ስደደን!” ሲሉ ለመኑት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አጋንንቱም፦ ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን ብለው ለመኑት። ሂዱ አላቸው።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 8:31
9 Referencias Cruzadas  

ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


ከእነርሱም ርቆ የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር።


እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ፤ በውሃም ውስጥ ሞቱ።


“ወደ እሪያዎቹ እንድንገባ ስደደን፤” ብለው ለመኑት።


በታላቅ ድምፅም እየጮኸ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለ፤


ስለዚህ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ! ደስይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፤ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”