ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
ማቴዎስ 8:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ጸሐፊም ቀርቦ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አንድ የአይሁድ ሃይማኖት መምህር ወደ እርሱ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፤ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ጸሐፊ መጥቶ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አንድ የሕግ መምህር፥ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፥ “መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ ልከተልህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ጻፊም ቀርቦ፦ መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ አለው። |
ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ወገን ከሁሉ ያልወጣ፥ የእርሱ ገንዘብ ከሆነውም ሁሉ ያልተለየ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው? ጸሓፊስ ማን ነው? ይህን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን?
እናንተም ወደምሄድበት ትሸኙኝ ዘንድ ምንአልባት የሆነውን ቀን ያህል በእናንተ ዘንድ እቈይ፥ ወይም እከርም ይሆናል።