“አዎን ይገብራል” አለ። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ሆይ! ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥና ግብር ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸው? ወይስ ከእንግዶች?” አለው።
ማቴዎስ 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት ጐራ ሲል የጴጥሮስ ዐማት በትኵሳት ታምማ ተኝታ አገኛት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ አማቱ በትኩሳት ታማ ተኝታ አያት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስ ዐማት አተኲሶአት ታማ እንደ ተኛች አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤ |
“አዎን ይገብራል” አለ። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ሆይ! ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥና ግብር ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸው? ወይስ ከእንግዶች?” አለው።
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።