ማቴዎስ 4:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከገሊላም ከዐሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም የተነሣ ከገሊላ፣ ከ “ዐሥር ከተማ”፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ማዶ የመጡ ብዙ ሰዎች ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከገሊላ፥ ከዐሥሩ ከተሞች፥ ከኢየሩሳሌም፤ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከገሊላ ምድርና ከዐሥሩ ከተሞች ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ፥ ከዮርዳኖስም ወንዝ ማዶ የመጡ ብዙ ሰዎች ኢየሱስን ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። |
ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤ ብዙዎችም ሰምተው ተገረሙና “እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው?
ከእነርሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመላው ይሁዳና ከኢየሩሳሌም፥ ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርቻ ትምህርቱን ሊሰሙ፥ ከደዌአቸውም ሊፈወሱ የመጡት ከሕዝቡ ወገን እጅግ ብዙዎች ነበሩ።