እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?” ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
ማቴዎስ 26:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ “ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ያጠለቀ፥ እኔን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋራ እጁን ከወጭቱ ውስጥ ያጠለቀው ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ከእኔ ጋር እጁን በሳሕኑ ውስጥ የሚያጠልቀው፥ እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ከእኔ ጋር በሳሕኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም መልሶ፦ ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ያጠለቀ፥ እኔን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ነው። |
እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?” ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
ነገር ግን ይህን የምናገር ስለ ሁላችሁ አይደለም፤ የመረጥኋቸው እነማን እንደ ሆኑ እኔ አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚመገብ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።