ማቴዎስ 25:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፤ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ አልጠየቃችሁኝም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ አልጠየቃችሁኝም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዳ ሆኜ መጥቼ ነበር፥ አልተቀበላችሁኝም፤ በቤታችሁ ታርዤ ነበር፥ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ ነበር፥ አልጠየቃችሁኝም፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፥ “በጎችን በትናችኋል፤ አባርራችኋቸውማል፥ አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ! እንደ ሥራችሁ ክፋት እጐበኛችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።
እነርሱ ደግሞ ይመልሱና ‘ጌታ ሆይ! ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም?’ ይሉታል።
ከጥቂት ቀን በኋላም ጳውሎስ በርናባስን፦“እንግዲህስ እንመለስና የእግዚአብሔርን ቃል ባስተማርንባቸው ሀገሮች ያሉትን ወንድሞች እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው።
ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ።
በገባዖንም ገብተው ያድሩ ዘንድ ወደዚያ አቀኑ። ገብተውም በከተማው አደባባይ በተቀመጡ ጊዜ ወደ ቤቱ የሚያስገባቸውና የሚያሳድራቸው አልነበረም።