ማቴዎስ 25:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የማይረባ ባሪያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማይረባውን ባርያ በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት፤ በዚያ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የማይረባ አገልጋይ ግን በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። |
አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን፥ ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት በአያችኋቸው ጊዜ እናንተን ወደ ውጭ ያወጡአችኋል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”