“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔርም እንደምቀና ታያለህ” አለው። ከእርሱም ጋር በሰረገላው አስቀመጠው።
ማቴዎስ 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በል ድርሻህን ይዘህ ሂድ፤ ለአንተ የሰጠሁትን ያህል በመጨረሻ ለመጣውም ሰው መስጠት እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአንተ የሆነውን ውሰድና ሂድ፤ ለአንተ የሰጠሁህን ያህል ለዚህ ለኋለኛውም ልሰጠው ፈለግሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ድርሻህን ይዘህ ሂድ፤ ለአንተ የሰጠሁትን ያኽል ለዚህ ለኋለኛውም ልሰጠው ፈቀድኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን? |
“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔርም እንደምቀና ታያለህ” አለው። ከእርሱም ጋር በሰረገላው አስቀመጠው።
“እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።
መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።