እጁንም ጫነባቸውና ከዚያ ሄደ።
እጁንም ከጫነባቸው በኋላ ከዚያ ስፍራ ተነሥቶ ሄደ።
እጆቹን ጫነባቸውና ከዚያ ሄደ።
እጁንም ከጫነባቸው በኋላ ከዚያ ስፍራ አልፎ ሄደ።
መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፤ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፤ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
ነገር ግን ኢየሱስ “ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና” አለ፤
እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ “መምህር ሆይ! የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ” አለው።
አቀፋቸውም እጁንም ጭኖ ባረካቸው።
የማያምን ባል በሚስቱ ይቀደሳልና፤ የማታምን ሚስትም በባልዋ ትቀደሳለችና፤ ያለዚያማ ልጆቻቸው ርኩሳን ይሆናሉ፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው።
ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል።