Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማቴዎስ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን ኢየሱስ “ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና” አለ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኢየሱስም፣ “ሕፃናት ወደ እኔ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፤ አትከልክሏቸውም፤ መንግሥተ ሰማይ እንደ እነዚህ ላሉት ናትና” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ አለ “ሕፃናቱን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ኢየሱስም፦ “መንግሥተ ሰማይ እንደነዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሉአቸው” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን ኢየሱስ፦ ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 19:14
18 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ሐ​ቅን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ገረ​ዘው።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


እንዲህም አለ “እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።


እጁንም ጫነባቸውና ከዚያ ሄደ።


ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።


“ንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።


ኢየሱስ ግን አይቶ ተቈጣና “ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና።


እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም፤” አላቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በአ​እ​ምሮ እንደ ሕፃ​ናት አት​ሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃ​ናት ሁኑ፤ በዕ​ው​ቀ​ትም ፍጹ​ማን ሁኑ።


እር​ሱም፦ እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ እን​ግ​ዲህ የወ​ይን ጠጅ​ንና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥን አት​ጠጪ፥ ርኩስ ነገ​ር​ንም አት​ብዪ፤ ልጁ ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና አለኝ” ብላ ተና​ገ​ረች።


እር​ስ​ዋም፥ “አዶ​ናይ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! የባ​ር​ያ​ህን መዋ​ረድ ተመ​ል​ክ​ተህ ብታ​ስ​በኝ፥ ለባ​ር​ያ​ህም ወንድ ልጅ ብት​ሰጥ ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም አይ​ጠ​ጣም። ምላ​ጭም በራሱ ላይ አይ​ደ​ር​ስም” ብላ ስእ​ለት ተሳ​ለች።


ሐና ግን ከእ​ርሱ ጋር አል​ወ​ጣ​ችም። ለባ​ል​ዋም፥ “ሕፃ​ኑን ጡት እስከ አስ​ጥ​ለው፥ ከእ​ኔም ጋር እስ​ኪ​ወ​ጣና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስ​ኪ​ታይ ድረስ አል​ወ​ጣም፤ በዚ​ያም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል” ብላ​ዋ​ለ​ችና።


እር​ስ​ዋም ከእ​ርሱ ጋር አንድ የሦ​ስት ዓመት ወይ​ፈን፥ እን​ጀራ፥ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴ​ሎም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገባች። ልጃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።


ሳሙ​ኤል ግን ገና ብላ​ቴና ሳለ የበ​ፍታ ኤፉድ ታጥቆ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያገ​ለ​ግል ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos