ማቴዎስ 18:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው “በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “በመንግሥተ ሰማይ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ሰዓት ደቀመዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው? ብለው ጠየቁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፦ “በመንግሥተ ሰማይ ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው፦ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? አሉት። |
እርስ በርሳችሁ በወንድማማችነት መዋደድ ተዋደዱ፤ የምትራሩም ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ መምህሮቻችሁንም አክብሩ።
በክርክርና ከንቱ ውዳሴን በመውደድ አትሥሩ፤ ትሕትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ።