ዐይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።
ቀና ብለው ሲመለከቱም ከኢየሱስ በቀር ሌላ ማንንም አላዩም።
ዐይኖቻቸውን በገለጡ ጊዜ ግን ከኢየሱስ በቀር ማንንም አላዩም።
እነርሱም ቀና ብለው ሲመለከቱ ከኢየሱስ በቀር ማንንም አላዩም።
ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።
ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፤ አትፍሩም፤” አላቸው።
ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ፤” ብሎ አዘዛቸው።
ድንገትም ዞረው ሲመለከቱ ከእነርሱ ጋር ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።
ቃሉም ከመጣ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ብቻውን ተገኘ፤ እነርሱ ግን ዝም አሉ፤ ያዩትንና የሰሙትንም በዚያ ጊዜ ለማንም አልተናገሩም።