ማቴዎስ 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዛሙርቱም “እንግዲህ ጻፎች ‘ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል፤’ ስለ ምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱም፣ “ታዲያ ጸሐፍት፣ አስቀድሞ መምጣት ያለበት ኤልያስ ነው ለምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀ መዛሙርቱም “ታዲያ ጻፎች ‘ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል’ ለምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም “ታዲያ፥ የሕግ መምህራን አስቀድሞ መምጣት ያለበት ኤልያስ ነው ለምን ይላሉ?” ሲሉ ኢየሱስን ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርቱም፦ እንግዲህ ጻፎች፦ ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል ስለ ምን ይላሉ? ብለው ጠየቁት። |
“እንኪያ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?” ብለው ጠየቁት፤ “አይደለሁም” አለ፤ “እንኪያ አንተ ነቢዩ ነህን?” አሉት፤ “አይደለሁም” አለ።
“እንኪያስ ክርስቶስን ካልሆንህ፥ ኤልያስንም ካልሆንህ፥ ነቢይንም ካልሆንህ ለምን ታጠምቃለህ?” ብለው ጠየቁት።