ማቴዎስ 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው “እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እናንተስ ለወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትሽራላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “እናንተስ ስለ ልማዳችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? ሲል መለሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተስ ወጋችሁን ለመጠበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለምን ታፈርሳላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ? |
ይህም ስለ ልብ ትሕትናና እግዚአብሔርንም ስለ መፍራት፥ ለሥጋ ስለ አለማዘን ጥበብን ይመስላል፤ ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለውም።
ለዚህ ዓለም ስሕተት፥ በክርስቶስ ሕግ ያይደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥርዐት ለከንቱ የሚያታልሉ ሰዎች በነገር ማራቀቅ እንዳያታልሉአችሁ፥ ተጠንቀቁ።