ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፤ ልቡም ዐመፅን ያደርግ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፥ የተራበችውንም ሰውነት ይበትን ዘንድ፥ የተጠማችንም ነፍስ ባዶ ያደርግ ዘንድ ከንቱን ያስባል።
ማቴዎስ 12:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን?” ብለው ጠየቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም አንድ እጁ ሽባ የሆነ ሰው ነበር፤ ኢየሱስን ሊከስሱት ምክንያት ፈልገው፣ “በሰንበት ቀን መፈወስ ተፈቅዷል?” ብለው ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ አንድ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ሊከሱትም ፈልገው “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን?” ብለው ጠየቁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም አንድ እጀ ሽባ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስን የሚከሱበትን ምክንያት የፈለጉ አንዳንድ ሰዎች “በሰንበት ቀን በሽተኛን መፈወስ ተፈቅዶአልን?” ሲሉ ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ፦ በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት። |
ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፤ ልቡም ዐመፅን ያደርግ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፥ የተራበችውንም ሰውነት ይበትን ዘንድ፥ የተጠማችንም ነፍስ ባዶ ያደርግ ዘንድ ከንቱን ያስባል።
በድለናል፤ ዋሽተናልም፤ አምላካችንንም መከተል ትተናል፤ ዐመፃን ተናግረናል፤ ከድተንሃልም፤ የኀጢአትንም ቃል ፀንሰን፤ ከልብ አውጥተናል።
ጽድቅን የሚናገር በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በከንቱ ነገር ታምነዋል፤ የማይጠቅማቸውንም ተናግረዋል፤ ኀጢአትን ፀንሰዋል፤ በደልንም ወልደዋል።
መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ በክንዱና በቀኝ ዓይኑ ላይ ይሆናል፣ ክንዱም አጥብቃ ትደርቃለች፥ ቀኝ ዓይኑም ፈጽማ ትጨልማለች።
የምኵራቡ ሹምም ጌታ ኢየሱስ በሰንበት ፈውሶአልና፤ እየተቈጣ መልሶ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፥ “ሥራችሁን የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች ያሉ አይደለምን? ያንጊዜ ኑና ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም።”
እንዲህም አላቸው፥ “ይህን ሰው ሕዝብን ያሳምፃል ብላችሁ ወደ እኔ አመጣችሁት፤ በፊታችሁም እነሆ፥ መረመርሁት፤ ግን እናንተ ካቀረባችሁት ክስ በዚህ ሰው ላይ ያገኘሁት አንዳች በደል የለም።
እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄሣር ግብር እንዳይሰጡ ሲከለክልና ሕዝቡን ሲያሳምፅ፥ ራሱንም የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስን ሲያደርግ አገኘነው።”
የሙሴ ሕግ እንዳይሻር ሰው በሰንበት የሚገዘር ከሆነ እንግዲያ ሰውን ሁለንተናውን በሰንበት ባድነው ለምን ትነቅፉኛላችሁ?
ከፈሪሳውያንም አንዳንዶች፥ “ይህ ሰው ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ሰንበትን አያከብርምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢኣተኛ ሰው እንዲህ ያለ ተአምራት ማድረግ እንዴት ይችላል?” አሉ፤ እርስ በርሳቸውም ተለያዩ።