ማቴዎስ 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ከሄዱ በኋላ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ወደ ምድረ በዳ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ሸንበቆ በነፋስ ሲወዛወዝ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ “ወደ ምድረ በዳ ምን ልታዩ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸምበቆ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ፥ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤ “ለመሆኑ ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ፦ ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? |
የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው?” አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ “ ‘ከሰማይ’ ብንል ‘እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤
እንግዲህ እንዴት እንደምትሰሙ አስተውሉ፤ ላለው ይሰጠዋል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።”
እንግዲህ በሽንገላቸው ያስቱ ዘንድ በሚተናኰሉ ሰዎች ተንኰል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ ወዲያና ወዲህ እየተፍገመገምንና እየተንሳፈፍን ሕፃናት አንሁን።