በእግዚአብሔርም ፊት ታቀርባቸዋለህ፤ ካህናቱም ጨው ይጨምሩባቸዋል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ያቀርቡአቸዋል።
ማርቆስ 9:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፤ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም ሁሉ በእሳት ይቀመማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መሥዋዕት በጨው እንደሚጠራ እያንዳንዱ ሰው በእሳት መጥራት አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል። |
በእግዚአብሔርም ፊት ታቀርባቸዋለህ፤ ካህናቱም ጨው ይጨምሩባቸዋል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ያቀርቡአቸዋል።
የምታቀርቡት ቍርባን ሁሉ በጨው ይጣፈጣል፤ የአምላክህም ቃል ኪዳን ጨው ከቍርባንህ አይጕደል፤ በቍርባናችሁ ሁሉ ላይ ጨው ትጨምራላችሁ።