ማርቆስ 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ጊዜም ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውኀም ጣለው፤ ቢቻልህ ግን እዘንልን፤ እርዳንም፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊገድለው ፈልጎ ብዙ ጊዜ እሳትም ውስጥ ውሃም ውስጥ፣ ይጥለዋል፤ የሚቻልህ ከሆነ ራራልን፤ ርዳንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊገድለው ፈልጎ ብዙ ጊዜ እሳትም ውስጥ ውሃም ውስጥ፥ ይጥለዋል፤ የሚቻልህ ከሆነ ራራልን፤ ርዳንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊገድለውም እየፈለገ ብዙ ጊዜ በእሳትና በውሃ ውስጥ ይጥለዋል፤ ግን አንዳች ነገር ማድረግ ብትችል እባክህ እዘንልን! እርዳንም!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ጊዜም ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውኃም ጣለው፤ ቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳንም አለው። |
ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ኢየሱስም “ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን?” አላቸው። “አዎን፥ ጌታ ሆይ!” አሉት።
ኢየሱስም አልፈቀደለትም፤ ነገር ግን “ወደ ቤትህ ወደ ቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው፤” አለው።