La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቃሉንም ይዘው “ከሙታን መነሣት ምንድር ነው?” እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም የተናገራቸውን ቃል በልባቸው አሳደሩት፤ ነገር ግን፣ “ከሙታን መነሣት” ምን ማለት እንደ ሆነ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም የተናገራቸውን ቃል በልባቸው አሳደሩት፤ ነገር ግን፥ “ከሙታን መነሣት” ምን ማለት እንደሆነ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቃሉንም ሰምተው በልባቸው ያዙት፤ ይሁን እንጂ “ይህ ከሞት መነሣት ምን ማለት ይሆን?” እያሉ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቃሉንም ይዘው፦ ከሙታን መነሣት ምንድር ነው? እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።

Ver Capítulo



ማርቆስ 9:10
15 Referencias Cruzadas  

ወን​ድ​ሞ​ቹም ቀኑ​በት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ ይጠ​ብ​ቀው ነበር።


ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ! ይህ ከቶ አይደርስብህም፤” ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።


እነርሱም “ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንዲገባው ጻፎች ስለ ምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት።


እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።


ከተራራውም ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አስ​ቀ​ድ​መው ይህን ነገር አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከከ​በረ በኋላ በዚያ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ፥ ይህ​ንም እንደ አደ​ረ​ጉ​ለት ትዝ አላ​ቸው።


የኤ​ፌ​ቆ​ሮ​ስን ትም​ህ​ርት ከተ​ማሩ ፈላ​ስ​ፋ​ዎች መካ​ከ​ልና ረዋ​ቅ​ያ​ው​ያን ከሚ​ባ​ሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላ​ስ​ፎ​ችም የተ​ከ​ራ​ከ​ሩት ነበሩ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም፥ “ይህ ለፍ​ላፊ ምን ሊና​ገር ይፈ​ል​ጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ስለ መነ​ሣ​ቱም ሰብ​ኮ​ላ​ቸ​ዋ​ልና የአ​ዲስ አም​ላክ ትም​ህ​ር​ትን ያስ​ተ​ም​ራል” አሉ።