ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
ኢየሱስም ስለ እርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው።
ኢየሱስም፦ “ስለ እኔ ለማንም እንዳትናገሩ፤” ብሎ አስጠነቀቃቸው።
ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።
ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።
“ለማንም አትንገሩ፤” ብሎ አዘዛቸው፤ እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት።
ወደ ቤቱም ሰደደውና “ወደ መንደሩ አትግባ፤ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር፤” አለው።
ከተራራውም ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።
ይህንም ለማንም እንዳይናገሩ ገሠጻቸውና ከለከላቸው።