ማርቆስ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፤ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ የሰዎችን ወግና ሥርዐት ታጠብቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ የሰዎችን ወግና ሥርዓት ትጠብቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ እናንተ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። |
ፈሪሳውያንና ጻፎችም “ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ፤” ብለው ጠየቁት።