ማርቆስ 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለ “ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ እንዲህ አለ፤ “ከሰው የሚወጣ ያ ሰውን ያረክሰዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጥሎም፥ እንዲህ አለ፤ ከሰው የሚወጣ ያ ሰውን ያረክሰዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም እንዲህ አለ፦ “ሰውን የሚያረክሱት ከሰው ልብ የሚወጡት ነገሮች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። |
አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዐመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፤ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፤ በገሃነምም ይቃጠላል።