ማርቆስ 6:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ትቷቸው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ትቷቸው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ተለይቶ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። |
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
ጳውሎስም እንደ ገና በወንድሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጠ፤ በሰላምም ሸኙትና ወደ ሶርያ በባሕር ተጓዘ፤ ጵርስቅላና አቂላም አብረውት ነበሩ፤ ስእለትም ነበረበትና በክንክራኦስ ራሱን ተላጨ።
ከዚህም በኋላ በሚሸኙት ጊዜ፥ “እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንደገና እመለሳለሁ፤ አሁን ግን የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም ላደርግ እወዳለሁ” አላቸው፤ ከኤፌሶንም በመርከብ ሄደ።