የእስራኤል ቤት ሆይ! ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
ማርቆስ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ከዚያ ወጥተው፤ ሰዎች ንስሓ እንዲገቡ ሰበኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ከዚያ ወጥተው፤ ሰዎች ንስሓ እንዲገቡ ሰበኩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተላኩትም ከዚያ ወጥተው፥ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ አስተማሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ፥ ብዙ አጋንንትንም አወጡ፥ |
የእስራኤል ቤት ሆይ! ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።
የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚች ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፋረዱአታል፤ ያሳፍሩአታልም፤ ዮናስ በሰበከላቸው ጊዜ ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ።
እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት ደስታ ይሆናል።”
እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኙ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በሰማያት ፍጹም ደስታ ይሆናል።
ይህንም በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፥ “እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሓን ሰጣቸው እንጃ” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፥ “ንስሓ ግቡ፤ ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ ኀጢአታችሁም ይሰረይላችኋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ትቀበላላችሁ።
ወደ እግዚአብሔር መመለስንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለአረማውያን እየመሰከርሁ፤
አስቀድሜ በኢየሩሳሌምና በደማስቆ ላሉት፥ ለይሁዳ አውራጃዎችም ሁሉ ነገርኋቸው፤ ለአሕዛብም ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ፥ ለንስሓቸውም የሚገባ ሥራን ይሠሩ ዘንድ አስተማርኋቸው።