ማርቆስ 3:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና “እነሆ እናቴ ወንድሞቼም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያው ወደ ተቀመጡትም በመመልከት፣ እንዲህ አለ፤ “እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም እየተመለከተ፥ “እነሆ! እናቴና ወንድሞቼ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዙሪያው ተቀምጠው ወደነበሩት እየተመለከተ፥ “እነሆ! እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና፦ እነሆ እናቴ ወንድሞቼም። |
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ፥ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።
ልጁ በብዙዎች ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውንና የመረጣቸውን እነርሱን ልጁን ይመስሉ ዘንድ አዘጋጅቶአቸዋል።