ማርቆስ 14:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጣም፤ ተኝተውም አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም “ስምዖን ሆይ! ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመልሶም ሲመጣ ደቀ መዛሙርቱን ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው፣ “ስምዖን ሆይ፤ ተኝተሃልን? አንድ ሰዓት እንኳ ነቅተህ መጠበቅ አቃተህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሶም ሲመጣ ደቀ መዛሙርቱን ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው፤ “ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንድ ሰዓት እንኳ ነቅተህ መጠበቅ አቃተህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተመልሶ በመጣ ጊዜ፥ ተኝተው አገኛቸው፤ ስለዚህ ጴጥሮስን፦ “ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት እንኳ ልትነቃ አልቻልክምን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጣም ተኝተውም አገኛቸው፥ ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን? |
እግሮችህ ሮጠው ይደክማሉ፤ ፈረሶችን ለምን ታስጌጣለህ? በሰላምም ምድር ላይ ለምን ትታመናለህ? በዮርዳኖስስ ጩኸት ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?
የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ” አለው።