La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 13:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፤ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህም ቤቱን ለባሮቹ ትቶ፣ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፣ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህም ቤቱን ለአገልጋዮቹ ትቶ፥ እያንዳንዱን አገልጋይ በየሥራ ድርሻው ላይ አሰማርቶ፥ በረኛው ነቅቶ እንዲጠብቅ አዝዞ የሄደውን ሰው ይመስላል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህም፥ ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ አገር የሄደውን ሰው ይመስላል፤ እርሱም እያንዳንዱን አገልጋይ በልዩ ልዩ የሥራ ኀላፊነት ላይ መደበ፤ ዘበኛውንም ተግቶ እንዲጠብቅ አዘዘው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፥ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።

Ver Capítulo



ማርቆስ 13:34
17 Referencias Cruzadas  

የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።”


ለእ​ርሱ በረ​ኛው ይከ​ፍ​ት​ለ​ታል፤ በጎ​ቹም ቃሉን ይሰ​ሙ​ታል፤ እር​ሱም በጎ​ቹን በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ አው​ጥ​ቶም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል።


ስለ​ዚ​ህም ግብር ታገ​ቡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ለዚህ ሥራ የተ​ሾሙ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸ​ውና፤


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋጋ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ት​ቀ​በሉ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለክ​ር​ስ​ቶስ ትገ​ዛ​ላ​ች​ሁና፤


ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦