ማርቆስ 12:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች፤” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን ከጕድለቷ ያላትን፣ መኖሪያዋን ሁሉ ሰጠች።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን በድህነት ዐቅሟ ያላትን ሁሉ አውጥታ ለመኖሪያ የሚሆናትን እንዳለ ሰጠች።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎቹ ሁሉ የሰጡት ካላቸው ሀብት የተረፋቸውን ነው፤ እርስዋ ግን ድኻ ሆና ሳለች ምንም ሳታስቀር ያላትን ሁሉ ሰጠች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው። |
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨናንቁት ነበር፤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረች ሴት መጣች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ለባለመድኀኒቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያድናት የቻለ ማንም አልነበረም።
ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?