ሐናንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ግማሽ አስላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ለሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።
ማርቆስ 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም ሌላውን ባሪያ ወደ እነርሱ ላከ፤ እርሱንም ወግረው ራሱን አቈሰሉት፤ አዋርደውም ሰደዱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም ሌላ ባሪያ ላከ። እነርሱም ራሱን ፈንክተውና አዋርደው መለሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገናም ሌላ አገልጋይ ላከ። እነርሱም ራሱን ፈንክተውና አዋርደው መለሱት”፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገና ባለቤቱ ሌላ አገልጋይ ላከ፤ ገበሬዎቹ ይህንንም በድንጋይ ፈንክተውና አዋርደው ሰደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳግመኛም ሌላውን ባሪያ ወደ እነርሱ ላከ እርሱንም ወግረው ራሱን አቈሰሉት አዋርደውም ሰደዱት። |
ሐናንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ግማሽ አስላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ለሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።