እንዲህም አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።
ማርቆስ 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ “ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው?” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ከቆሙት አንዳንድ ሰዎች፣ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ከቆሙት አንዳንድ ሰዎች፥ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ጊዜ እዚያ ቆመው ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ፦ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ፦ ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው አሉአቸው። |
እንዲህም አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።