እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
ማርቆስ 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም “ሙሴስ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ እንዲፈታት ፈቀደ፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ሙሴማ የፍችውን ጽሕፈት ጽፎ እንዲፈታት ፈቅዷል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “ሙሴማ የፍች ወረቀት ጽፎ እንዲፈታት ፈቅዷአል” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “ሙሴማ የፍችዋን የምስክር ወረቀት ሰጥቶ እንዲፈታት ፈቅዶአል፤” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ሙሴስ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ እንዲፈታት ፈቀደ አሉ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? አንቺም ከብዙ እረኞች ጋር አመንዝረሻል፤ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።