እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፤” አላቸው።
ማርቆስ 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ማንም ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ በርሷ ላይ ያመነዝራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “ማንም ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ በእርሷ ላይ ያመነዝራል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሴት የሚያገባ በሚስቱ ላይ አመንዝሮአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤ |
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፤” አላቸው።
ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትሆናለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥታለች፤ ለሌላ ወንድ ብትሆንም አመንዝራ አትባልም።
ሚስት በራስዋ አካል ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ባል በራሱ አካል ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።