በቤትም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር ጠየቁት።
እንደ ገና ወደ ቤት በገቡ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ይህንኑ አንሥተው ጠየቁት።
እንደገና ወደ ቤት በገቡ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ ይህንኑ አንሥተው ጠየቁት።
ወደ ቤት በተመለሱ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ጉዳይ እንደገና ኢየሱስን ጠየቁት፤
እርሱም “ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል፤
እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።”
ብቻውንም በሆነ ጊዜ በዙሪያው የነበሩት ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ስለ ምሳሌው ጠየቁት።
ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ “እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው?” ብለው ብቻውን ጠየቁት።
ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ “በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።