ሚልክያስ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም፣ መላው ሕዝባችሁም ስለምትሰርቁኝ የተረገማችሁ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ ሰርቃችሁኛልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ፥ ሕዝቡም ሁሉ ከእኔ ስለምትዘርፉ የተረገማችሁ ሆናችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። |
እንዲህም አለኝ፦ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፣ የሚሰርቅ ሁሉ በእርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል፥ በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል።
ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፣ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።
የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኀጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቍጣ አልወረደምን? እርሱም ብቻውን ቢበድል በኀጢአቱ ብቻውን ሞተን?”