ኤልሳዕም በሬዎቹን ተወ፤ ኤልያስንም ተከትሎ ሄደ፥ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። እርሱም“ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው።
ሉቃስ 9:59 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌላውንም፥ “ተከተለኝ” አለው፤ እርሱ ግን፥ “አቤቱ፥ በፊት ሄጄ አባቴን እንድቀብረው ፍቀድልኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላውን ሰው ግን፣ “ተከተለኝ” አለው። ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፤ አስቀድሜ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላውንም፦ “ተከተለኝ፤” አለው። እርሱ ግን፦ “ጌታ ሆይ! መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላውንም ሰው “ተከተለኝ!” አለው። ሰውየው ግን “ጌታ ሆይ! መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ። |
ኤልሳዕም በሬዎቹን ተወ፤ ኤልያስንም ተከትሎ ሄደ፥ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። እርሱም“ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ሙታኖቻቸውን ይቀብሩ ዘንድ ሙታንን ተዉአቸው፤ አንተ ግን ሂድና የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ” አለው።