ሉቃስ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምትገቡበት ቤት በዚያ ተቀመጡ፤ እስክትሄዱም ድረስ ከዚያ አትውጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ከተማ እስከምትወጡ ድረስ መጀመሪያ በገባችሁበት በማንኛውም ቤት ቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማናቸውም በምትገቡበት ቤት በዚያ ተቀመጡ፤ ከዚያም ካረፋችሁበት ቤት ወጥታችሁ ሂዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእንግድነት በምትገቡበት ቤት ሁሉ ከዚያ መንደር ወጥታችሁ እስክትሄዱ ድረስ በዚያው ቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማናቸውም በምትገቡበት ቤት በዚያ ተቀመጡ ከዚያም ውጡ። |
እንዲህም አላቸው፥ “በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ወርቅም ቢሆን፥ ሁለት ልብስም ቢሆን ለመንገድ ምንም አትያዙ።
እርስዋም ከቤተ ሰቦችዋ ጋር ተጠመቀች፤ “ለእግዚአብሔር አማኝ ካደረጋችሁኝስ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እደሩ” ብላ ማለደችን፤ የግድም አለችን።