La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 9:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ህም በኋላ ከእ​ርሱ ሲለዩ ጴጥ​ሮስ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “መም​ህር፥ ሆይ፥ እዚህ ብን​ኖር ለእኛ መል​ካም ነው፤ ሦስት ሰቀ​ላ​ዎ​ች​ንም እን​ሥራ፤ አን​ዱን ለአ​ንተ፥ አን​ዱ​ንም ለሙሴ፥ አን​ዱ​ንም ለኤ​ል​ያስ” አለው፤ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቅም ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰዎቹም ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ እዚህ ብንሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤ አንዱ ለአንተ፣ አንዱ ለሙሴ፣ አንዱም ለኤልያስ ይሆናል” አለው፤ የሚናገረውንም አያውቅም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእርሱም ሁለቱ ሰዎች በተለዩ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ “አቤቱ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ፥ አንድም ለሙሴ፥ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤” አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁለቱ ሰዎች ከኢየሱስ ተለይተው በሄዱ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ አንድ ለአንተ፥ አንድ ለሙሴ፥ አንድ ለኤልያስ የሚሆኑ ሦስት ዳሶች እንሥራ!” አለው፤ ጴጥሮስ ይህን ሲናገር የሚለውን አያውቅም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።

Ver Capítulo



ሉቃስ 9:33
13 Referencias Cruzadas  

እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤ እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤ ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ።


ወደ ሕዝቡም ሲደርሱ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ


ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፦ “ጌታ ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ፤” አለ።


ኢየሱስ ግን “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አላቸው።


ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “መም​ህር፥ ሌሊ​ቱን ሁሉ ደክ​መ​ናል፤ የያ​ዝ​ነ​ውም የለም፤ ነገር ግን ስለ አዘ​ዝ​ኸን መረ​ቦ​ቻ​ች​ንን እን​ጥ​ላ​ለን” አለው።


ይህ​ንም ሲና​ገር ደመና መጣና ጋረ​ዳ​ቸው፤ ወደ ደመ​ና​ውም በገቡ ጊዜ ፈሩ።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ በስ​ምህ ጋኔን ሲያ​ወጣ ያየ​ነው አንድ ሰው አለ፤ ከእ​ኛም ጋር አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ህ​ምና ከለ​ከ​ል​ነው፤” አለው።


ፊል​ጶ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳ​የ​ንና ይበ​ቃ​ናል” አለው።


በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።