ሉቃስ 8:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከያዕቆብና ከዮሐንስ፥ ከብላቴናይቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር ሌላ ሰው ይገባ ዘንድ አልፈቀደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሲገባም ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና እናት በቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ቤቱም በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስና ከያዕቆብ ከዮሐንስም፥ ከልጅቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር እንዲገባ አልፈቀደም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፥ ከዮሐንስ፥ ከያዕቆብ፥ ከልጅትዋ አባትና እናት በቀር ሌላ ማንም ከእርሱ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤትም ሲገባ ከጴጥሮስና ከያዕቆብ ከዮሐንስም ከብላቴናይቱም አባትና እናት በቀር ማንም ከእርሱ ጋር ይገባ ዘንድ አልፈቀደም። |
እነርሱም እነዚህ ናቸው፦ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን፥ ወንድሙም እንድርያስ፥ ያዕቆብና ዮሐንስ፥ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ።
ሁሉም እያለቀሱ ዋይ ዋይ ይሉላት ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን፥ “አታልቅሱ፤ ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።
ከዚህም ነገር በኋላ በስምንተኛው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ጴጥሮስን፥ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞአቸው ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
ጴጥሮስም ሁሉን ካስወጣ በኋላ ተንበርክኮ ጸለየ፤ ወደ በድንዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እርስዋም ዐይኖችዋን ገለጠች፤ ያንጊዜም ጴጥሮስን አየችው፤ ቀና ብላም ተቀመጠች።