La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 7:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሴቶች ከወ​ለ​ዱ​አ​ቸው መካ​ከል ከመ​ጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ የሚ​በ​ልጥ ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ግን የሚ​ያ​ን​ሰው ይበ​ል​ጠ​ዋል።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እላችኋለሁ፤ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴቶች ከወለዱአቸው ሰዎች መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

Ver Capítulo



ሉቃስ 7:28
13 Referencias Cruzadas  

ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።


በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ ሁሉ​ንም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ በውኃ አጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ግን የሚ​በ​ል​ጠኝ የጫ​ማ​ውን ማሰ​ሪያ እንኳ ልፈ​ታ​ለት የማ​ይ​ገ​ባኝ ይመ​ጣል፤ እርሱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ሳ​ትም ያጠ​ም​ቃ​ች​ኋል።


እነሆ፥ መን​ገ​ድ​ህን በፊ​ትህ የሚ​ጠ​ርግ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ዬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፥ ተብሎ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ለት ይህ ነው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ቀራ​ጮ​ችም በሰሙ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጻድቅ ነው አሉት፤ የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ተጠ​ም​ቀው ነበ​ርና።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በስሜ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሕፃን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፥ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል፤ ራሱን ከሁሉ ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ርግ እርሱ ታላቅ ይሆ​ናል።”