ሉቃስ 6:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንደርም ወይንን አይለቅሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛፍ ሁሉ በፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾኽ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፤ ከቀጋ ቍጥቋጦ የወይን ፍሬ አይቈረጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፤ ከአጣጥ ቁጥቋጦም ወይን አይቈርጡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛፍ ሁሉ በፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾኽ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፤ እንዲሁም ከእሾኻማ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ አይለቀምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃልና፤ ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፥ ከአጣጥ ቍጥቋጦም ወይን አይቈርጡም። |
እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥