ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ጠበቅሁት፤ ነገር ግን እሾህን አፈራ።
ሉቃስ 6:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ፍሬን የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለም፤ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ክፉ ዛፍም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መልካም ዛፍ ሆኖ ሳለ መጥፎ ፍሬ የሚያፈራ የለም፤ እንዲሁም መጥፎ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ዛፍ የተበላሸ ፍሬ አያፈራምና፤ እንዲሁም የተበላሸ ዛፍ መልካም ፍሬ አያፈራም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መልካም ዛፍ መጥፎ ፍሬ አያፈራም፤ እንዲሁም መጥፎ ዛፍ መልካም ፍሬ አያፈራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉ ፍሬ የሚያደርግ መልካም ዛፍ የለምና፥ እንዲሁም መልካም ፍሬ የሚያደርግ ክፉ ዛፍ የለም። |
ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ጠበቅሁት፤ ነገር ግን እሾህን አፈራ።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
እኔ የተመረጠች ወይን፥ ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንዴት መራራ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?
ወንድምህንም፦ ወንድሜ ሆይ፥ ታገሥ፤ በዐይንህ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ ልትለው እንደምን ትችላለህ? አንተ ግን በዐይንህ ውስጥ ያለውን ምሰሶ አታይም፤ አንተ ግብዝ፥ አስቀድሞ ከዐይንህ ምሰሶውን አውጣ፤ ከዚህ በኋላ በባልንጀራህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።